ተደጋግመው የሚነሱ ጥያቄዎች

መርሀግብሮች፣ ካርታዎች እና በራሪ ጽሑፎች

ተረኛው የዲሲ ሰርኩሌተር (DC Circulator) አውቶብስ መቼ እንደሚደርስ እንዴት ማወቅ እችላለሁኝ?

የዲሲ ሰርኩሌተር የአውቶብስ መድረሻ ሰዓት መተግበሪያ አፕ መተግበሪያ አውቶብ አሁን የት እንደደረሰ ይጠቁሞታል፣ እና የእርስዎ መቆሚያ ቦታ ላይ መቼ እንደሚደርስ ይነግሮታል። የአውቶብስ መድረሻ ጊዜን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት https://bustime.dccirculator.com ይጎብኙ። https://dccirculator.com/ride/rider-tools/interactive-map ላይ ሊገኝ የሚችለውን፣ ተቀያያሪ የካርታ ባህሪ በመጠቀም እርስዎ የሚገኙብት አድርሻ ላይ ቅርብ የሆነውን የዲሲ ሰርኩሌተር መንገድ ይወቁ። 

የሰርኩሌተሩን የአውቶብስ መርሀግብር የት ማግኘት እችላለሁኝ?

የዲሲ ሰርኩሌተር አውቶብሶች እያንዳንዱ 10 ደቂቃ ላይ ይደርሳል፣ ምንም ዓይነት መርሀግብሮች አያስፈልጉም! የእኛን የስራ ሰዓታት መረጃ ለማየት፣ የ መርሀግብር ገጽ ይጎብኙ። 

የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታን የት ማግኘት እችላለሁኝ?

የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታ ለህትመት ዝግጁ የሆነ ፒዲኤፍ (PDF) ፋይል እና የመረጃ በራሪ ጽሑፍ ወረቀት እዚህ ጋር በመሄድ ማውረድ ይችላሉ።  

የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታ በደብዳቤ እንዲላክልኝ እንዴት ማድረግ እችላለሁኝ?

የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታ እና በራሪ ጽሑፍ ወረቀት በ CommuterPage.com ነጻ በራሪ ጽሑፍ በደብዳቤ መርሀግብር በኩል በማንኛውም የዩኤስ አድራሻ ላይ በጋራ ለመላክ ዝግጁ ናቸው። ለእርስዎ እንዲላክሎት ለማድረግ፣ የማዘዣ ገጹን ይጎብኙ እና ከምርጫ ምናሌው ላይ “ዲሲ ሰርኩሌተር ባስ” የሚለውን ይምረጡ። የሚገኙበትን አድራሻ ያስገቡ እና በራሪ ጽሁፉ ያለምንም ክፍያ ወደ መኖሪያ ቤትዎ ወይም ቢሮዎት ይላክሎታል።  

ለሆቴሌ ወይም ለንግድ ተቋሜ ካርታዎችን በጅምላ ማዘዝ እችላለሁኝ?

አዎ። ብዙ የታተሙ የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታዎች እና የመረጃ በራሪ ጽሑፎችን ለመጠየቅ፣ እባክዎ የእኛ ያግኙን ገጽ ላይ የሚገኘውን የኢሜይል ቅጽ ይሙሉ። ስምዎን እና የስራ ሁኔታዎን ይግለጹ እና ወኪላችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያገኞታል።  

የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታን በአካል በመምጣት የት መውሰድ እችላለሁኝ?

የታተሙ የዲሲ ሰርኩሌተር ካርታዎች እና የመረጃ በራሪ ጽሑፎች እያንዳንዱ ሰርኩሌተር አውቶብስ ውስጥ ይኖራሉ እና በሜትሮ ዲሲ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ የበራሪ ጽሁፍ መደርደሪያዎች ላይ ጭምር ይገኛሉ።   

የአውቶብስ ሹፊሮቹ ቀጣዩቹን መጫኛና ማውረጃ ቦታዎችን ይናገራሉ?

ሁሉም የዲሲ ሰርኩሌተር አውቶብሶች የተገጠሙ ድምጽ ማጉያዎች አሏቸው። ማስታወቂያዎችን መስማት የማይችሉ ከሆነ፣ የአውቶብሱ ሰራተኛ የማቆሚያ ቦታውን በድጋሚ እንዲነግሮት ወይም ድምጹን ከፍ እንዲያደርገው መጠየቅ ይችላሉ።  

ተደራሽነት

በዲሲ ሰርኩሌተሮች ላይ ዌልቼር እና ተሽከርካሪ ሞተሮችን ይስተናገዳሉ?

ሁሉም አውቶብሶች ልቼሮችን እና ሞተር ተሽከርካሪዎችን ለማስተናገድ የተዘጋጁ ናቸው፣ እና ዝቅተኛ ወለል ያላቸው እና ለተደራሽነት የዝቅተኛ ወለል መገጣጠሚያ ያላቸው ናቸው። ልቸሮች የተዘጋጁ እያንዳንዱ ቦታዎች ላይ የዌልቼር ማሰሪያ ተገጥሞላቸዋል። ለአካለስንኩላን ተሳፊሪዎች የበለጠ ዝርዝር መረጃ ለማግኘት፣ የእኛን ተደራሽነት ገጽ ይጎብኙ። በአንድ ጊዜ ላይ ሁለት ዌልቼሮች ወይም ሞተር ተሽከርካሪዎች ብቻ ማስተናገድ ይችላል። 

ወደ ውጭ ማየት ለማይችሉ ሰዎች በሰርኩሌተር አውቶብስ ውስጥ የማቆሚያ ቦታዎቹ ይነገራሉ?

የእኛ ፖሊሲ የሚደነግገው እያንዳንዱ የአውቶብስ ሹፌር በእያንዳንዱ አውቶብስ ላይ የተገጠሙትን የሕዝብ ማሳወቂያ ድምጽ ማጉያዎች በመጠቀም ቀጣዩን የመጫኛና ማውረጃ ቦታ እንዲጠቁሙ ነው። የሹፌሩን ማስታወቂያ መስማት የማይችሉ ከሆነ፣ የማቆሚያ ቦታውን አድራሻ እንዲደግም/እንድትደግም ለሹፌሩ መጠየቅ ወይም ድምጹን ከፍ እንዲያደርግ/እንድታደርግ መጠየቅ ይችላሉ።  

የክፍያ እና የታሪፍ መረጃ

በዲሲ ሰርኩሌተር ላይ መጓዝ ምን ያህል ያስከፍላል?

የዲሲ ሰርኩሌተር የአንድ ሰው፣ የአንድ ጉዞ መነሻ የክፍያ ታሪፍ ተመን $1 ነው። ለአዛውንቶች እና ለተማሪዎች ቅናሽ ይሰጣል። ለዝርዝሩ የ የታሪፍ ክፍያ እና ተመን ገጽ ይጎብኙ። 

WMATA፣ VRE እና MARC ወርሃዊ ማለፊያዎች ናቸው እና ትራንስሊንክ ካርዶች (TransitLink Cards) በሰርኩሌተር ላይ ነፃ ሽግግር ለማድረግ ይፈቀዳሉ?

የዲሲ ሰርኩሌተር ለ7-ቀን $17.50 የ WMATA የክፍለ ሀገር አውቶብስ ማለፊያዎችን ይቀበላል፣ ይሄ በስማርትትሪፕ ካርድ ላይ ብቻ ሊጫኑ ይችላሉ። ለበለጠ መረጃ፣ እዚህ ይጎብኙ፦ https://www.wmata.com/fares/farecard-options.cfm 

የዲሲ ሰርኩሊተር አውቶብሶች ላይ መጓዝ ክፍያ ያስከፍላል?

የዲሲ ሰርኩሌተር የአንድ ሰው፣ የአንድ ጉዞ መነሻ የክፍያ ታሪፍ ተመን $1 ነው። ለአዛውንቶች እና ለተማሪዎች ቅናሽ ይሰጣል። በስማርትትሪፕ (SmarTrip) በኩል የሚከፍሉ ከሆነ በዲሲ ሰርኩሊተር አገልግሎት ላይ ለሚሰሩ ሌሎች አውቶብሶች ላይ የሁለት-ሰዓት ጊዜ ያህል ነፃ የማሸጋገሪያ ዕድል ይሰጣል። ለዝርዝሩ https://dccirculator.com/fares ላይ ይጎብኙ። 

የመኪና ማቆሚያ ስፍራ እና መንገድን ማግኘት

የዲሲ ሰርኩሌተር ላይ ለመሳፈር መኪናዬን የት ማቆም እችላለሁኝ?

የዲሲ ሰርኩሌተር መንገዶች ከመኪናዎቻቸው ላይ በመውጣት የሚሳፈሩባቸው ለደንበኞች የተዘጋጁ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች የሉትም። በዲሲ ውስጥ መኪና እንዴት እንደሚያቆሙ አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት የሚሹ ከሆነ፣ የ goDCgo.com የመኪና ግብዓቶች ገጽ ጠቃሚ ዋቢ ማድረጊያ ግብዓት ነው። 

የትኛው የሰርኩሌተር መንገድ እኔ የምፈልገው አድራሻ ላይ ቅርብ እንደሆነ በምን ማወቅ እችላለሁኝ?

አዲሱ እና የተሻሻለው የእኛ ተግባቢ ካርታ እርስዎ የሚገኙበት ቦታ ላይ ቅርብ የሆነውን የዲሲ ሰርኩሌተር የአውቶብስ መጫኛና ማውረጃ ቦታን ይጠቁሞታል። በቀላሉ አድራሻዎን እዚህ ላይ ያስገቡ።  

የግል ዕቃዎችን ይዞ መሳፈር

ብስክሌቴን አውቶብስ ላይ ይዤ መሳፈር እችላለሁኝ?

አዎ! እያንዳንዱ የዲሲ ሰርኩሌተር አውቶብስ ከውጭ በኩል ፊቱ ላይ ሁለት ብስክሌቶችን የመስቀያ ቦታ አለው። በአውቶብሱ ላይ እንዴት ብስክሌትዎን እንደሚጭኑ ለማወቅ የአውቶብስ ሹፌሮቹን ይጠይቁ። ሙሉ መመሪያዎችን እና ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት የእኛን በሰርኩላር ላይ ብስክሌቶች ገጽ ይመልከቱ። 

የልጅ ጋሪዎቼን አውቶብስ ላይ ይዤ መሳፈር እችላለሁኝ?

የልጅ ጋሪዎችን አውቶብሱ ውስጥ ይዞ መግባት ይፈቀዳል እና መታጠፍ አያስፈልጋችውም። በአውቶብሱ ውስጥ በአንድ ጊዜ ላይ ሁለት ጋሪዎች (በአንድ ሰው አንድ ጋሪ) ብቻ ይፈቀዳል።  የእኛን በሰርኩሌተር ውስጥ ጋሪዎች ገጽ ይጎብኙ። 

አውቶብስ ላይ ስሳፈር ጋሪዎቼን ክፍት እንደሆኑ ማስቀመጥ እችላለሁኝ?

ጎማዎቹ የተቆለፉ ከሆነ እና አስተማማኝ የሆነ የጉዞ ሁኔታ ለመፍጠር በቂ የሆነ ክፍት ቦታ ካለ ብቻ ልጆች በጋሪው ውስጥ መቀመጥ ይችላሉ። የዲሲ ሰርኩሌተር ሹፌሮች አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ተሳፋሪዎችን ጋሪዎቻችውን እንዲያጥፉ እና ከመቀመጫው ስር እንዲያስቀምጡ የማዘዝ ስልጣን አላቸው። 

ሞተር አውቶብስ ላይ ይዤ መሳፈር እችላለሁኝ?

ሞተሮች በሹፌሩ ፈቃድ እና በአውቶብስ ውስጥ ባለው ክፍት ቦታ ሁኔታ መሰረት በአውቶብስ ላይ ይዞ መውጣት ይችላል። በአንድ ተሳፋሪ አንድ ሞተር ብቻ ይፈቀዳል። ሞተሮች አውቶብሱ ላይ ባትሪ ሊሞላባቸው አይችሉም። 

ለማዳ እንስሳቶች በዲሲ ስርኩሌተር አውቶብስ ውስጥ ይፈቀዳሉ?

አዎ፣ የቤት እንስሳቶች በዲሲ ሰርኩሌተር አውቶብስ ላይ እንዲሳፈሩ ይፈቀድላቸዋል፣ ሆኖም ግን፣ ሁሉም የቤት እንስሳቶች በመደርደሪያ ወይም ማቀፊያ ቤት ውስጥ መቀመጥ አለባቸው በተለይ ለእንሳ ማጓጓዣነት የተሰሩ ዕቃዎችን መጠቀም እና በጉዞ ላይ መታሰር አለባቸው። ሁሉም አገልግሎት ሰጪ እንስሳቶች ያለምንም  መደርደሪያ ወይም ማቀፊያ ቤት አስፈላጊነት እንዲጫኑ ይፈቀድላቸዋል። 

የጠፉ እና የተገኙ ዕቃዎች

በአውቶብስ ውስጥ ዕቃ የጣልኩኝ ከሆነስ?

በአውቶብስ ውስጥ ዕቃ የጣሉ ከሆነ፣ የእኛን የምንገኝበት ቅጽ ይሙሉ፣ ቅጹ እዚህ የጠፉ ዕቅዎችን ያግኙ እና ይውሰዱ ላይ ይገኛሉ። እባካዎ የተጓዙበት የጉዞ መስመር፣ ሰዓት እና የጠፋውን ዕቃ(ዎች) ማብራሪያ ይፃፉልን። በተቻለን መጠን ዕቃውን ለማግኘት እና መልሰን ለእርስዎ ለመስጠት እንሞክራለን። 

ዕቃዎቼን የት ሄጄ መውሰድ እችላለሁኝ?

የዲሲ ሰርኩሌተር ሹፌር፣ የ RATPDev አድራሻ 1710 17th Street NE Washington, DC 20002 ላይ ነው። 

መዘግየቶች

ማንኛውም ዓይነት የአውቶብስ መዘግየት ያለ ከሆነ እንዴት አውቃለው?

ፈጣን የሆኑ አዲስ የአገልግሎት መረጃዎችን ለማግኘት የዲሲ ስርኩሌተርን በትዊተር (Twitter) አድራሻ @dccirculator ላይ ይከታተሉ፣ ወይም ይሄንን ድረገጽ በመከተል፣ የእኛ የትዊተር መረጃ መጋቢ የሁኔታዎችን ደረጃ በመነሻ ድረገጻችን ላይ ያሳውቃል። ችግር ያለባቸውን መንገዶች በተመለከተ ይበልጥ መረጃ ለማግኘት፣ የድር ጣቢያችን ‘ማንቂያዎች እና ምክሮች’ (‘Alerts & Advisories’) ገጽን በዚህ ላይ ያግኙ https://dccirculator.com/ride/rider-tools/service-alerts 

የእኔ አውቶብስ ከመርሀግብሩ ውጪ ቆሟል። ለምንድን ነው?

አገልግሎት የሚሰጥበት ሙሉ ቀን ላይ የተወሰኑ ጊዜዎች ላይ፣ የዲሲ ስርኩሌተር አውቶብሶች አገልግሎት ከመስጠት ሊቆሙ ይችላሉ – አንዳንዴ ለአጭር ጊዜ ያህል አገልግሎት ከመስጠት ሊቆሙ ይችላሉ።  እረፍት መውሰድ የ10-ደቂቃ ክፍተቶችን ለማስቀጠል አስፈላጊ ናቸው እና እርስዎ ወጥ የሆነ ጊዜውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላሉ። የዲሲ ሰርኩሌተሮች የሚሰሩት በጊዜ ሰሌዳ ሳይሆን በሰዓት ክፍተት ስለሚሰሩ፣ አውቶብሶቹን ማቆም እያንዳንዱ መንገድ ላይ ያሉ አውቶብሶች ቅርብ ለቅርብ ተቀራርበው እንዳይጓዙ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም፣ ለሹፌሮቻችን የሚያስፈልጋችውን ንቃት ለማግኘት እና አውቶብሱን በሚገባ እንዲሾፍሩ ለማድረግ የሚያስችለውን እረፍት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል።  

የደንበኛ ተሞክሮ

የዲሲ ስርኩሌተሮች የአየር መቆጣጠሪያ ተገጥሞላቸዋል?

የራይደርሺፕ ፍላጎቶችን ለማሳካት፣ ከ 2005 ጀምሮ አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው የቫን ሁል (Van Hool) አውቶብሶች አሉ። እነዚህ አውቶብሶች ሲፈበረኩ ጊዜ ጠንካራ የሆነ የአየር መቆጣጠሪያ አልተገጠመላቸውም ነበር ነገር ግን ቆይቶ ኤሲ ተገጥሞላቸዋል። አንዳንድ ጊዜ ላይ የዲሲ የበጋ የአየር ንብረት ከአቅም በላይ ይሆንባቸዋል። 

ሁሉንም የቫን ል አውቶብሶች ከስምሪት ለማስወጣት እየሞከርን ነው። ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ፣ በሙቀት ቀናት ወቅት፣ መኪናውን በሚገባ ሁኔታ የሚያቀዘቅዙ የአየር መቆጣጠሪያዎች ሙሉ ለሙሉ የተገጠመላቸው ብዙ አዲስ አውቶብሶችን አስገብተናል።